በኢትዮጵያ የመሬት መንቀጥቀ ተከሰተ

ኢትዮ እማማ
በሆሳህና ከተማ ትናንት እሁድ የመሬት መንቀጥቀ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ዛሬ አስታወቀ።
በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት (3:15 pm) ላይ በመሬት መንቀጥቀጥ መለኪያ 5.3 ሬክተር ስኬል በሆሳህና ከተማ ውስጥ መከሰቱን በዩንቨርስቲው የመሬት መንቀጥቀ ኤክስፐርት ዶ/ር አታላይ አየለ ገልጸዋል።

እንደ ዶ/ሩ ገለጻ የመሬት መንቀጥቀጡ የሆሳህናን ከተማ 30 ኪሎ ሜትር መሸፈኑ ታውቋል። አንዳንድ የዓይን እማኞች እንደገለጹት ከሆነ የመሬት መንቀጥቀጡ ለ19 ሰከንድ የቆየ ሲሆን በአንዳንድ ያረጁ ቤቶች ላይ ጉዳት ከማምጣቱ በስተቀር በከተማው የሚገኙ ፎቆች የመሬት መንቀጥቀጡን እንደተቋቋሙና መጠነኛ የመሰነጣጠቅ ጉዳት ከመድረሱ በሰተቀር የከፋ ጉዳት አለመድረሱን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በጅማ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ከቀትር በኋላ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በዩኒቨርሲቲው 26 ተማሪዎች ላይ መጠነኛ የአካል ጉዳት አድርሷል።ጉዳቱ ሊደርስ የቻለው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋውን ሲሰሙ ተማሪዎች ከነበሩባቸው የመኝታ ክፍሎች ለመውጣት ሲገፋነው ተብሏል።በሕንጻ ላይም የመሬት መንቀጥቀጡ መጠነኛ ጉዳት ማድረሱን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።