ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
ፍቅር ለይኩን (ከደቡብ አፍሪካ)
የነፃነት አርበኛ፣ የይቅርታ አባት፣ የፍቀር ተምሳሌት፣ የአይበገሬነትና የፅኑ መንፈሥ ባለቤት፣ የመለያየትንና የዘረኝነትን ፅኑ ግንብ በማይለወጥ ፍቅር ያፈረሱ፣ የሠላም መልዕክተኛ፣ የሰው ልጆች ሁሉ የአንድነት ምልክት፣ … ወዘተ በሚሉ ቅጥያ ስሞች በሚታወቁት በዛሬው የ92 ዓመት አዛውንት ኔልሰን ማንዴላ የትግልና የፖለቲካ ሕይወት ውስጥ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያላት ሥፍራ በእጅጉ የተለየ ነው።