የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡና ደንበኞች በሞባይል ሒሳብ አሞላል ተመረዋል

“በሞባይል ስልክ ሒሳብ የማስገባት ችግር ለሁለት ሳምንት ይቆያል” ኢትዮ ቴሌኮም

ካለፈው ወር ጀምሮ የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ሒሳብ ወደ ተንቀሳቃሽ ስልክ (ሞባይል) ካርድ መሙላትና ማስገባት አስቸጋሪና አዳጋች በመሆኑ፣ የዲፕሎማቲክ ኅብረተሰቡን ጨምሮ በርካታ ደንበኞች ቅሬታቸውን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡