የአፍሪቃ ህብረት እና የኮሚሽኑ ፕሬዚደንት ምርጫ ሂደት

የአፍሪቃ ህብረት ዛሬ ለህብረቱ ኮሚሽን ፕሬዚደንትነት ሥልጣን ምርጫ አካሂዶ ነበር። ለምርጫው የኮሚሽኑ ፕሬዚደንት ዣን ፒንግ እና የደቡብ አፍሪቃ የሀገር አስተዳደር ሚንስትር ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ በዕጩነት ቀርበው ነበር።