ሸራተን አዲስ ከሠራተኛው ጋር ‹‹ለመደራደር ፍቃደኛ አይደለሁም›› አለ
በታምሩ ጽጌ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የለገሀር አካባቢ ፖሊስና ዓቃቤ ሕግ በጋራ በመሆን የሸራተን አዲስ ሆቴል ኃላፊዎችንና የሠራተኞች ተወካዮችን ለማደራደር ለትናንትና ከጧቱ 4 ሰዓት በፖሊስ ጣቢያው ጽሕፈት ቤት ቀጠሮ ሰጥተው የነበረ ቢሆንም፣ የሆቴሉ ኃላፊዎች እንደማይደራደሩ በጠበቃቸው በኩል በመግለጻቸው ሳይሳካ ቀረ፡፡