ለአንድ ሲኒ ቡና 6,500 ብር ቅጣት

በሚኪያስ ሰብስቤ

ለአንድ ሲኒ ቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ደረሰኝ ሳይቆረጥ ግብይት ፈጽሟል በሚል ባለፈው ሳምንት የጥፋተኝት ውሳኔ የተላለፈበት ቶሞካ ቡና ላኪ፣ አምስት ሺሕ ብር እንዲቀጣ ሲል የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ አሥረኛ ወንጀል ችሎት ከትናንት በስቲያ ወሰነ፡፡