ናሆም ሪከርድስ ለሚካያ በኃይሉ 100 ሺሕ ብር ካሣ እንዲከፍል ተወሰነበት

 

(በሚኪያስ ሰብስቤ)

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስምንተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ናሆም ሪከርድስ የሚካያ በኃይሉን ሁለት ዘፈኖች የአርቲስቷን የቅጂ መብት በመጣስ በማባዛቱና በማከፋፈሉ፣ 100 ሺሕ ብር የሞራል ካሳ እንዲከፍል ባለፈው ሣምንት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡