በሐዋሳ ቅ/ገብርኤል ውስጥ ብጥብጥ የፈጠሩ ፍርድ ቤት ቀረቡ
- ያሬድ አደመ እና ዓለምነህ ሽጉጤ አሉበት፤
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 10/2010፤ ኀዳር 1/2003 ዓ.ም)፦ እሑድ ጥቅምት 28 ቀን 2003 ዓ.ም በሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በተፈጠረው ዐምባጓሮ በሕጋዊ የገዳሙ ሰንበት ት/ቤት አባላት ላይ ከፍተኛ የድብደባ ጉዳት ያደረሱት ያሬድ አደመ እና ዓለምነህ ሽጉጤን ጨምሮ 11 ያህል ሰዎች በትናንትናው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ በተጎጂ ቤተሰቦች በተመሠረተው ክስ ፖሊስ ሀገረ ስብከቱን በማወክ እና የክልሉን ሰላም በማደፍረስ ሁከት በፈጠሩት ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ እና ቀሪ ሁከተኞችን ለማደን የጠየቀው ዘጠኝ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ጥያቄ የፍርድ ቤቱን ይሁንታ አግኝቷል፡፡ ከሁከቱ በኋላ እሑድ ዕለት ረፋድ ላይ ወደ አዲስ አበባ ለመሔድ ሲዘጋጅ የተያዘውን ያሬድ አደመን፤ አባቶችን፣ የሐዋሳ የፍትሕ እና ልማት ኮሚቴ አባላትን እና ማኅበረ ቅዱሳንን በስም እየለየ የሚያክፋፋ የቅስቀሳ ወረቀት ሲበትን በማግስቱ ሰኞ የተያዘውን ዓለምነህ ሽጉጤን ለማስመለቀቅ ጓደኞቻቸው በየአቅጣጫው የሚያደርጉትን ጥረት ቀጥለውበታል፡፡
(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)