በዱባይ ሻርጃ ለአንድ ወር የሚዘልቅ የስብከተ ወንጌል ጉባኤ ሊካሄድ ነው
- በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሊባኖስ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ አህጉረ ስብከታቸውን እያወኩ በሚገኙት ሕገወጦች ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ቋሚ ሲኖዶሱን በደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡
- ከሕገ ወጦቹ አንዱ የሆነው እና በአገር ውስጥ በስም ማጥፋት ወንጀል ክስ የተመሠረተበት በጋሻው ደሳለኝ ነገ ወደ ሥፍራው ይጓዛል፤
- "የዱባይ ቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን" በሚል ጉባኤ ለማካሄድ የተዘጋጁት አካላት ሕገ ወጥ መሆናቸው ተገልጧል፤
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 14/2010፤ ኅዳር 5/2003 ዓ.ም)፦ በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሊባኖስ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሥር በሚተዳደረው በዱባይ – ሻርጃ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለአንድ ወር የሚዘልቅ የስብከተ ወንጌል ጉባኤ ተዘጋጀ፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር የስብከተ ወንጌል ጉባኤውን ለማስተዋወቅ ‹‹ሕዝቤ ሆይ ወደ ቤትህ ግባ›› በሚለው የነቢዩ ኢሳይያስ መሪ ቃል ባወጣው ፖስተር ላይ እንደተገለጸው፣ ጉባኤው የሚካሄደው በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ ተባርኮ ወደ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የገባው የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ታቦት ኅዳር 12 ቀን 2003 ዓ.ም ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ የሚደረገውን ክብረ በዓል መሠረት አድርጎ ነው፡፡
(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)
