ቤትህን አስተካክል
"ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤…።
ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።" (ኤር.፬፡፳፪)
(አብርሃም ሰሎሞን)
በእጅህ ያኖርኩትን የብርሃን ፀዳል መቅረዙን
ከስፍራው መጥቼ ሳልወስደው፣
ከዝናም በኋላ ደመናት ሳይሸሹ ፀሐይ
ሳትጨልም ቀኑን ሳልጋርደው፣
ከማሳው ያለውን ፍሬ አልባ ዘርህን ማለዳ
መጥቼ ከእርሻው ላይ ሳልነቅለው፣
የሰጠሁህን ሀብት ከመዳፍ ከጉያህ በአንድ
ጀምበር እድሜ አውጥቼ ሳልጥለው፣
እፍ ያልኩበትን ነፍስ ከውስጥህ ለይቼ
ወደነበረበት ስፍራ ሳልመልሰው፣
አእምሮ አለህና ነቅተህ ተዘጋጅተህ አደራህን
ፈጽም አስተውል አንተ ሰው።
(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)
