የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመለሱ
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 26/2010፤ ኅዳር 17/2003 ዓ.ም)፦ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ከኅዳር ስምንት ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት በማቆም እና ከምግብ ቤቱ አገልግሎት በመከልከል ባነሷቸው ችግሮች አፈታት ላይ ስምምነት ተደረሰ፤ ደቀ መዛሙርቱም ከትናንት ኅዳር 18 ቀን 2003 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ በኮሌጁ የምግብ ቤት አገልግሎት መጠቀም መጀመራቸው ታውቋል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ከኮሌጁ አስተዳደር እና ቦርድ ጋራ ከስምምነት ላይ እንዲደርሱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር እና ደቀ መዛሙርቱ አቤቱታቸውን ካቀረቡላቸው የውጭ አካላት አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ናቸው፡፡
(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)