የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን የገንዘብ እና ንብረት ቆጠራ ላይ ጥብቅ መመሪያ ሰጠ
- ለሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ እና ለሥራ አስኪያጁ ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም አቀባበል ተደርጓል፡፡
- አጥቢያ አብያተ ክርስቲያኑ ለሀገረ ስብከቱ ፈሰስ ማድረግ የሚጠበቅባቸው የ58 ሚሊዮን ብር ዕዳ ያለባቸው ሲሆን ሀገረ ስብከቱ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ፈሰስ ማድረግ ከሚጠበቅበት የዘመኑ ገቢ የ13 ሚሊዮን ብር ጉድለት ተገኝቶበታል፡፡
- ‹‹ምእመናን ተቸግረው በሚሰጡት ገንዘብ መልሰው እንዲያዝኑ ልናደርጋቸው አይገባም፡፡›› (ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ)
- ‹‹ለቅጥር፣ ዕድገት እና ዝውውር አማላጅ የመላክ ጉዳይ አይቻለሁ፤ በግልጽ ማስታወቂያ በሚወጣው መሠረት ከሚፈጸመው በቀር በምልጃ የሚደረግ ነገር አይኖርም፡፡›› (ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም)
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 27/2010፤ ኅዳር 18/2003 ዓ.ም)፦ ትናንት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጥሪ በተደረገላቸው የአዲስ አበባ ገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤ ጸሐፊዎች፣ ሒሳብ ሹሞች፣ የስብከተ ወንጌል ሐላፊዎች እና የምእመናን ተወካዮች በተገኙበት በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለሆኑት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ እና ለሥራ አስኪያጁ ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም የአቀባበል እና የትውውቅ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡
(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)
