ፍርድ ቤቱ በጋሻው ደሳለኝን በነጻ አሰናበተ
(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 2/2010፤ ኅዳር 23/2003 ዓ.ም)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የድሬዳዋ ማእከል የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ የቀረበበት በጋሻው ደሳለኝ ከቀረበበት ክስ በነጻ ተሰናበተ፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ካውንስል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ ጠዋት ኅዳር 23 ቀን 2003 ዓ.ም ውሳኔ የሰጠው ተከሳሹ በጋሻው ደሳለኝ ሚያዝያ 19 ቀን 2002 ዓ.ም በሳባ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን፣ “አንድ ማኅበር አለ – ማኅበረ ቅዱሳን የሚባል፡፡ ደም አፍሳሽ ማኅበር፣ የወንድሞችን ደም በጣሳ እየተቀበሉ ለመጠጣት የተዘጋጁ. . .” በማለት ያሰማው ንግግር “አያስከስስም” በሚል ነው፡፡ ውሳኔው ጉዳዩን በሚከታተሉ ሌሎች የፍትሕ አካላት እና የሕግ ባለሙያዎች ዘንድ ከፈጠረው መደናገር የተነሣ በጥንቃቄ እየተጤነ እንደሆነ ተገልጧል፡፡ (Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)