ኢትዮጵያ ከተማ ቦታ አዋጅና ተቃዉሞዉ

የኢሕአዲግ መንግሥት ያወጣዉ አዋጅ መንግሥትን ባለርስት የኢትዮጵያ ሕዝብን ደግሞ ገባር ወይም ጪሰኛ የሚያደርግ ነዉ። የኢትዮጵያ መንግሥት የከተማ ቦታን በኮንትራት (በሊዝ) ለማከራየት ያወጣዉን አዋጅ የሐገሪቱ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አጣጥለዉ ነቀፉት።የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ የአንድነት መድረክ እንደ ፓርቲ ባወጣዉ መግለጫና ባለሥልጣናቱ በየፊናቸዉ በሰጡት አስተያየት እንዳስታወቁት የኢሕአዲግ መንግሥት ያወጣዉ አዋጅ መንግሥትን ባለርስት የኢትዮጵያ ሕዝብን ደግሞ ገባር ወይም ጪሰኛ የሚያደርግ ነዉ።አዲሱን ሕግ ከዚሕ በፊትም የተለያዩ ወገኖች አጥብቀዉ ተቃዉመዉታል። መንግሥት ግን ሕጉ ለደሐዉ ጠቃሚ ነዉ ባይ ነዉ። ያዳምጡ