በአውሮጳ ፓርላማ ጉባኤ ተካሄዴ፤ ሰቆቃ የተፈጸመባቸው የኦጋዴን ተወላጆች በስብሰባው ላይ የምስክርነት ቃል ሰጡ

በአገራችን ኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትንና በዘረኛው የወያኔ አምባገነንነት የተቀለበሰውን የዲሞክራሲ ግንባታ ሁኔታ የሚዳስስ ጉባዔ ከትናንትና በስቲያ ማክሰኞ ህዳር 29 ቀን 2003 ዓም በአውሮጳ ፓላማ ውስጥ መካሄዱን የግንቦት 7 ዘጋቢ ከስፍራው ከላከልን ዜና ለማወቅ ተችሎአል።

የታገተው ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ፤ በኦጋዴን እየተፈጸመ ካለው ሁኔታ አንጻር ሲቃኝ ወይንም በኢንግለዘኛው “Ethiopia’s stalled Democracy, A spotlight on the Ogaden ¨” በሚል ርዕስ በተካሄደው በዚህ ጉባ ዔ የአውሮጳ ፓርላማ ምክትል ፕሬዝዳንት ሚስተር ላሲዚሎ ቶከስ \ Laszlo Tokes \ን ጨምሮ የተለያዩ የፓርላማ አባላት እና የሰበ ዓዊ መብት ተሟጋቾች የተገኙ ሲሆን በቲል ቡርግ ዩኒቨርሲት የአለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ፕሮፈሰር የሆኑት ቤልጅየማዊው ፕሮፈሰር ዣን ዣንስ / Jan Jans/ እና በኡተሬክት ዩኒቨርሲት የህግ እና የሰብዓዊ መብት አስተማሪ የሆኑት አመሪካዊቷ ፕሮፈሰር ዶ\ር በርቤራ ላክበርግ /Barbara Lakeberg/ በየተራ አገራችን ውስጥ እየተካሄደ ስላለው የመብት ጥሰትና የስልጣን ብልግና ለጉባ ዔው ተሳታፊዎች አስረድተዋል።

የአውሮፓ ፓርላማ ምክትል ፕሬዝዳንት ሚስተር ላስዚሎ ቶኬስ ባደረጉት ንግግር የገዢው ፓርቲ ወታደሮች እና ሸማቂያን መካከል በሚደረገው ጦርነት ምክንያት የኦጋዴን ክልል ለእርዳታ ለጋሾችም ሆነ ለጋዜጠኞች ዝግ በመሆኑ የተነሳ በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሰቆቃ መጠን ሂሊና ልገምተው ከሚችለው በላይ ሊሆን እንደሚችል አውስተው፡ ቅርብ በሆነቺው አንዲት ከሰሃራ በታች ባለች አገር እንዲህ አይነት ወንጀል ሲፈጸም ዝም ብሎ መመልከት አይቻለንም ብለዋል። በመቀጠልም ከአውሮጳ እና አሜሪካ ለ እርዳታ ፈላጊዎች በየጊዜው የምንሰጠው ገንዘብ እርዳታውን በተገቢ መንገድ ለህዝቡ እንዲያከፋፍል በሚሰጠው መንግሥት መልሶ ተረጂውን ለማጥቃት ሥራ ላይ ሲውል ለጋሾች አጃችንን አጣምረን መመልከት የለብንም ካሉ ቦኋላ በተለይ የምንሰጠው እርዳታ ህዝቦችን ለማፈንና ለመግደል አላማ ሊውል በማይችልበት ሁኔታ መከፋፈሉን ፡ ለጋሾች ከፍተኛ ቁጥጥር እና ክትትል ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በቅርቡ በጸደቅቀው የሊዝቦን ስምምነት መሰረት አውሮጳ በውጪ ግንኙነት ፖሊሲዋ ከማንኛውም አገር ጋር የሚኖራት የ እርዳታና የልማት ትብብር የሰው ልጅ መብት መከበርን ማዕከል ያደረገ ፤ ፍትህና ዲሞክራሲ የመሳሰሉ ታሪካዊ የአውሮጳ ህብረት እሴቶች ለድርድር በማይቀርቡበት ሁኔታ መሆኑ በትክክል ስለተደነገገ የአውሮጳ ህብረትና በተለይም የአውሮጳ ኮሚሽን ለኢትዮጵያ የሚሰጠው እርዳታ በምን አይነት መስፈርት እንደሆነ ሊጠይቅ አስፈላጊም ከሆነ ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል ብለዋል ።

ሃሳባቸውን በነጻነት እንዳይገልጹ እገዳ የተደረገባቸው እና በአገራቸው ፖለቲካ ጉዳይ በነጻነት ለመሳተፍ እኩል እድል የተነፈጉ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለፍትህ ፤ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ የሚያደርጉት ትግል የአለም አቀፉ ድጋፊ ልነፈገው አይገባም ያሉት የአውሮጳ ህብረት ምክትል ፕረዝደንት ላስዚሎ፤ የሃንጋሪ እና የቼክ ህዝቦች በ1956 እና በ1958 አድርገውት በነበረው የነጻነት ትግል ወቅት የአለም አቀፉ ህብረተሰብ ትብብር ነፍጎአቸው ለግማሽ ምዕተ አመት ያህል በከፍተኛ አምባገነናዊ ሥር ዓት ሥር እንዲማቅቅ ተደርጎ አንደነበር አውስተው የኢትዮጵያ ህዝብ ለለውጥ የሚያደርገው ትግል አንደ ያኔው ችላ ሊባል አይገባም ብለዋል።

ወያኔ በኦጋዴንና በተቀሩት የኢትዮጵያ ግዛቶች እየፈጸመ ያለው አፈናና ጭቆና በተለያዩ ፖለቲከኞችና ምሁራን በተዳሰሰበት በዚህ ጉባዔ ላይ፡ ተጋባዥ ተናጋሪ የነበሩት አለም አቀፍ የአናሳ ብሄረሰቦችና መንግሥት አልባ ዜጎች ጉዳይ ተከታታይ ድርጀት ዋና ጸሃፊ ሚስተር ማሪኖ ቡሳዳቺኒ /Marino Busdachin/ ፤ አምባገነንነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እርቃኑ እየወጣ የመጣው የመለስ ዜናዊ ሥር ዓት፡ ስልጣንን መከታ በማድረግ በሙስናና በዝርፊያ የተጨማለቀ ሆኖአል ከማለት አልፈው፡ የአውሮጳ ግብር ከፋይ ህዝብ በአገሩ በደረሰበት የኢኮኖሚ ውድቀት ቀደም ሲል ለማህበራዊ አገልግሎት ከሚያስተዳድሩት መንግስታት የሚሰጠው በጀት እየተቀነሰ በመጣበት በአሁኑ የችግር ወቅት እንደመለስ ዜናዊ ለመሳሰሉት የሰው ልጅ መብት ረጋጮች የስልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ የሚሆን እርዳታ ያለማቋረጥ ሲሰጥ ከማየት በላይ እኛ የአውሮጳ ግብር ከፋዮችን ሊያበሳጭ የሚችል የፖለቲካ ውሳኔ ሊኖር አይችልም ብለዋል ።

በዕለቱ ጉባኤ ላይ ቻናል ፎር የተባለው የ ኢንግሊዝ ቴለቪዝን ጣቢያ ከ2 አመት በፊት በኦጋዴን ስላለው ሰብ ዓዊ የመብት ጥሰት የቀረጸውና ለህዝብ ይፋ አድርጎት የነበረው ፊልም የታየ ሲሆን፤ በ15 ዓመት አፍላ ዕድሜዋ የኦጋዴን ነጻነት ተዋጊዎችን ትርዳላችሁ በሚል ክስ በወያኔ ጦር እስራት፤ ግርፋትና አስገድዶ የመድፈር ወንጀል የተፈጸመባት ፋጡማ የተባለች ሴት ልጅ ስለተፈጸመባት ሰቆቃ የሰጠቺው ምስክርነት ተደምጦአል። እንዲሁም በግርፋት ብዛት ሁለት እግሮቹ ለሽባነት የተዳረገው ሰው በዊንቼር መቀመጫ ተገፍቶ የምስክርነት ቃሉን ለመስጠት በቦታው የነበረ ቢሆንም በጉባ ኤው ከ2 ሰዓት ከሩብ በላይ መራዘም ምክንያት ዕድል እንዳላገኘ ሆኖም የተፈጸመበትን ሰቆቃ የሚገልጽ በጽሁፍ የተዘጋጄ ዶክመንት ለግባዔው አዘጋጆችና የአውሮጳ ፓርላማ ባለስልጣናት መሰራጨቱን አዘጋጆቹ ለዘጋቢያችን መግለጻቸውን ለማወቅ ተችሎአል።