በሱማሊያ የኢትዮጵያ ጦር ሰፈር በአጥፍቶ ጠፊዎች ተጠቃ!

አልሸባብ 10 ወታደሮች ገደልኩ ብሏል

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2004 ዓ.ም. January 25, 2012)፦ በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ጠቅላይ ሰፈር ላይ የአልሸባብ አጥፍቶ ጠፊ በሚኒባስ ሙሉ የታጨቁ ቦምቦች ማፈንዳቱ ተዘገበ። በጥቃቱ 10 የኢትዮጵያ ወታደሮች መግደሉን አልሸባብ ገለጸ።