በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በተከሰሱት እነ አንዱዓለም አራጌ ላይ ብይን ተሰጠ
በግንቦት 7 አሸባሪ ድርጅት ውስጥ አመራርና አባል በመሆን የአገሪቱን ፖለቲካ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሕገ መንግሥታዊ ተቋማትን በኃይል ለማናጋት ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል በሚል ተጠርጥረው በሽብር ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው፣ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ ስምንት በአገር ውስጥ ሆነው ክሳቸውን በመከታተል ላይ ያሉና በሌሉበት ክሳቸው በመታየት ላይ የሚገኙ ተከሳሾች፣ ተጠርጥረው የተከሰሱበትን የሽብር ወንጀል እንዲከላከሉ ትናንትና ብይን ተሰጠ፡፡