በአፋር ክልል ለታገቱት ጀርመናዊያን አርዱፍ ኃላፊነት ወሰደ
‘5ቱ ጎብኝዎች የሞቱት በኢትዮጵያ መንግስት ጥይት ነው’ አርዱፍ
Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 14 ቀን 2004 ዓ.ም. January 23, 2011)፦ ባለፈው ሳምንት ለ5 ጎብኝዎች ሞት ምክንያት ለሆነው እና ለ27 ጎብኝዎች ላይ ለተቃጣው ጥቃት በህወሀት መራሹ የኢትዮጵያ ወታደሮችና በአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (አርዱፍ) መሀከል በተነሳ ጦርነት መሆኑንና ታጋቾቹ ሁለት ጀርመናዊያን በእጁ እንደሚገኙ አርዱፍ አስታወቀ።