የዘረኛው የወያኔ አገዛዝ አፈና በኢትዮጵያውያን ላይ መበርታቱ የትጥቅ ቡድኖችን እያጠናከረ ነው ተባለ
በተለይ ከግንቦት 15ቱ የምርጫ ተውኔት በኋላ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከፓርላማው ውስጥ ፈጽሞ እንዲጠፉ መደረጉ የትጥቅ ቡድኖችን እያጠናከረ ነው ሲል ጅማ ታይምስ የተባለው የዜና ድረ-ገጽ ዘግቧል።
ድረ-ገጹ ሁለት የፖለቲካ ተንታኞችን በመጥቀስ፥ ህዝቡ፣ በተለይም ወጣቱ፣ በህጋዊ ትግል ያለውን እምነት በከፍተኛ ደረጃ እንዳጣ እና ይህም አገዛዙን ለመዋጋት ነፍጥ ያነሱ ቡድኖችን እየረዳ መሆኑን ዘግቧል። የፖለቲካ ተንታኞቹ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንቅስቃሴዎቻቸውን መጨመራቸውን እንደ ማስረጃ ጠቅሰዋል።
ኦነግ በቅርቡ በወያኔ አገዛዝ ላይ ባካሄዳቸው ሁለት ጥቃቶች በአስርት የሚቆጠሩ ወታደሮችን መግደሉ እና በርካቶችን ማቁሰሉን እንደገለጸ መዘገባችን ይታወሳል። ኦብነግ ደግሞ ባለፉት በርካታ ወራት የተለያዩ ድሎችን ማስመዝገቡን ሲገልጽ የቆየ ሲሆን፤ ባለፈው ሳምንት 35 ወታደሮችን መግደሉን በመግለጫው አስታውቋል።