ወድቆ በተነሳው ባንዲራ! አትቀልዱብን!!
ተመስገን ደሳለኝ
…ባለመሆንና በመሆን መካከል
ሰው አይሻገረው፣ አለ ትልቅ ገደል።
የማይሆነው ነገር፣ ምን ጊዜም አይሆንም
የሆነውም ነገር ከቶ አይለወጥም።…
‹‹የኮሌጅ ቀን ግጥሞች›› (ተገኝ የተሻወርቅ-1950ዓ.ም) ፐ-እንዴት ያለ ግጥም ነው! ከተፃፈ ከ54 አመት በኋላም ሳይበርድ ሳይነፍስበት የእኝንዘመኑን ገላጭ ነው። ፕሮፓጋንዳውን ገላጭ ነው። የፖለቲካውን ቅጥፈት ገላጭ ነው። የስርዓቱን ጉምነት ገላጭ ነው። በአጠቃላይኢህአዴግን ገላጭ ነው። አጋላጭም ነው።