አላሙዲ በአሜሪካ ተለጣፊ የስፖርት ፌዴሬሽን ሊያቋቁሙ ነው
አዲሱ ፌዴሬሽን (ESFNA-ONE) ተብሏል
አቶ አብነት የስፖርት ክለቦችን ለመደለል ገንዘብ መበተን ጀምሯል
Ethiopia Zare (ሐሙስ ጥር 3 ቀን 2004 ዓ.ም. January 12, 2011)፦ የሰሜን አሜሪካ ስፖረት ፌደሬሽን የሚያካሂደው አመታዊ የስፖርት ውድድር 28ኛ አመታዊ ዝግጅቱን በዳላስ ቴክሳስ እንደሚያካሂድ ይፋ ማድረጉ የሚታወቅ ሲሆን በሼህ መሀመድ አላሙዲ ወዳጅ አቶ አብነት የሚመራ አዲስ ፌደሬሽን ተቋቁሞ ሌላ የስፖርት ውድድር በዋሽንግተን ዲሲ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ መሆኑ ታወቀ።