ፍትሕ ሚኒስቴር ከሼክ አል አሙዲ የባንክ ሒሳብ እንዳይከፈለው ታገደ
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሰባተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ስም ከሚገኝ ሒሳብ 905‚158.06 ዶላር ወጪ አድርጐ ለፍትሕ ሚኒስቴር እንዲከፍል ያስተላለፈው የአፈጻጸም ውሳኔ፣ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመታገዱ የአፈጻጸም ሒደቱ ቆሞ መዝገቡ እንዲዘጋ ታህሳስ 11 ቀን 2004 ዓ.ም. ውሳኔ አስተላለፈ፡፡