ዲሞክራሲን ያያችሁ? (ክፍል 2)

ሉሉ ከበደ

በዲሞክራሲያዊ ስርዓት የዜጎች መብት

በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ ዜጎች ማንም የማይነጥቃቸው፤ መንግስት የማይቸራቸው የማይነሳቸው፤ የአለም አቀፍ ህግ ጥበቃና ዋስትና ያላቸው መብቶች አሏቸው። ማንኛውም ሰው የኔ የሚለውን የግሉን እምነት የመያዝ የመከተል መብት አለው። የሚያስበውን የመናገር፤ የመጻፍ፤ ሙሉ መብት አለው። ማንም ሰው ማንንም ሰው እንዲህ አስብ፤ እንዲህ እመን፤ እንዲህ ተናገር፡ እንዲህ አትናገር፤ ብሎ ሊነገረው አይችልም። ሊያዘውም ሊያስገድደውም አይችልም።