የሽብር ተጠርጣሪዎች አቤቱታ ያቀረቡበት “አኬልዳማ” ለፍርድ ቤት ከቀረቡት ማስረጃዎች ውጭ ነው ተባለ
– ዓቃቤ ሕግ ባቀረባቸው ማስረጃዎች ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ተሰጠ
በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ከተመሠረተባቸው 24 ተከሳሾች መካከል፣ በአገር ውስጥ ሆነው ክሳቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙት እነ አንዱዓለም አራጌ፣ “እኛ በሕግ ከለላ ሥር ሆነን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ‹‹አኬልዳማ›› በሚል ዘጋቢ ፊልም ስማችንን እያጠፋ ነው፤” በሚል ያቀረቡትን አቤቱታ የመረመረው ፍርድ ቤት፣ አኬልዳማን የሠሩት የፍርድ ቤቱን ማስረጃዎች ተጠቅመው ባለመሆኑ አቤቱታው ተቀባይነት እንደሌለው ታኅሣሥ 19 ቀን 2004 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡