የቦሌ ነዋሪዎችን ያስደነገጠው ወረዳ ተገምግሞ ይቅርታ እንዲጠይቅ ታዘዘ

‹‹የሊዝ አዋጅ በድጋሚ ሊታይ ይገባዋል›› ባለሙያዎች

በአፍሪካ ጎዳና (ቦሌ መንገድ) ወርቤክ ሕንፃና በቦስተን ዴይ ስፓ ሕንፃ ጀርባ የሚገኙ ባለይዞታዎች በሁለት ቀናት ውስጥ ቦታውን የማልማትም ሆነ ያለማልማት ፍላጎታቸውን እንዲያሳውቁ የጠየቀው የወረዳ ሁለት መሬት ልማት ባንክና ከተማ ማደስ ጽሕፈት ቤት፣ ያልተገባ ድርጊት ፈጽሟል በሚል መገምገሙንና ይቅርታ እንዲጠይቅ መታዘዙን ምንጮች አመለከቱ፡፡