የበረከት መጽሐፍ
ተስፋዬ ገብረአብ [email protected]
የበረከትን መጽሐፍ አነበብኩት …
በእውነቱ ህትመቱ ቆንጆ ነበር። ሽፋኑ እንደ ሃብታም ጉንጭ ይለሰልሳል። ከቻርልስ ዲክንስ ታዋቂ መጽሐፍ የተኮረጀ ቢሆንም ርእሱም ቢሆን አሪፍ ነው – የሁለት ምርጫዎች ወግ። የበረከትን መጽሐፍ ያሳተመው መሐመድ አሊ አልአሙዲ የተባለው ነጋዴ መሆኑን ፍትህ ጋዜጣ ላይ አንብቤ ነበር። መጽሐፉ 314 ገፆች እና 10 ምዕራፎች ይዞአል። ዋጋው 90 ብር ነው።