የሱዳን ነዳጅ ማጣሪያ ለዕድሳት ከመዘጋቱ በፊት የነዳጅ ኩባንያዎች ተጨማሪ ቤንዚን በርብርብ እንዲያስገቡ ታዘዙ

‹‹ሁኔታው ለቤንዚን ዋጋ ጭማሪ ሊዳርግ ይችላል›› የነዳጅ ኢንዱስትሪ ባለሙያ

(በኃያል አለማየሁ)

የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት የሱዳን ነዳጅ ማጣሪያ ለዓመታዊ ጥገና ሥራ ከማቋረጡ በፊት፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ የነዳጅ ኩባንያዎች ለወደፊት ፍጆታ የሚውል ቤንዚን በመረባረብ ከሱዳን ወደ አገር ውስጥ እንዲያመላልሱ አዘዘ፡፡