የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽንና ኃላፊዎች የፌዴራል ፍርድ ቤት አያዘንም አሉ
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለመሠረተው የፍትሐ ብሔር ክስ ማስረጃ እንዲልኩ ከፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የደረሳቸው የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአውሳ ዞን መስተዳድርና የሚሌ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ‹‹ክሱ መታየት ያለበት በክልላችን በመሆኑ ኃላፊዎችንም ሆነ የምርመራ መዝገቡን ለመላክ ፈቃደኛ አይደለንም›› ማለታቸውን ፌዴራል ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስታወቀ፡፡