አገሩማ የእኔ ነው… (ከተመስገን ደሳለኝ)

በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ለመፃፍ ያሰብኩት ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡ ..ጓደኞቼን መልሱልኝ… ብዬ በፃፍኩ በሳምንቱ ማለቴ ነው። ሆኖም በዛ ሳምንት በይደር የማይታለፍ አፋጣኝ መልስ የሚያስፈልገው ጉዳይ አጋጠመኝ። የ..አኬልዳማ.. ፊልም። ስለዚህ ይህን ርዕስ በይደር አልፌው የዛኛውን ሳምንት ለአኬልዳማ ሰዋሁት። እናም ጠቢቡ… ቦ ጊዜ ለኩሉ… እንዳለው ሁሉ እነሆም ጊዜው ሆነና የተዘለለው ርዕስ ተነሳ።