የሆስተሷ የቀድሞ ባለቤት መከላከያ ምስክሮቹን አሰምቶ ጨረሰ

– ‹‹ጥፋተኛ ነው አይደለም›› በሚለው ላይ ፍርድ ለመስጠት ተቀጥሯል

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በመሠረተበት ከባድ የአካል ማጉደል፣ የግድያ ሙከራና በሕግ የተከለከለ ሕገወጥ መሣርያ ይዞ መገኘት የወንጀል ክሶች፣ የመከላከያ ምስክሮቹን ሊያሰማ የነበረው የሆስተስ አበራሽ ኃይላይ የቀድሞ ባለቤት አቶ ፍስሐ ታደሰ፣ የመከላከያ ምስክሮቹን ለፍርድ ቤት ህዳር 27 ቀን 2004 ዓ.ም. አሰምቶ ጨረሰ፡፡