አረ ጎበዝ…! ኢትዮጵያ ከጃችን ማምለጧ ይሆን?!!

አትክልት አሰፋ (ከቫንኩቨር-ካናዳ)

ያሁኖቹ ቱጃሮችማ በቅጡ ይታወቃሉ። ብዙ ህዝብ መሀል ጣል ጣል ያሉ ስለሆኑ በደንብ ይታያሉ፤ አዲስ አበባም ሆነ ዋና ዋና የክ/ሀገር ከተሞች፤ ገጠርም ብትገቡ የማን ንብረት ምን እንደሆነ፤ የማን መኪና ታርጋ ቁጥር ለማን እንደተሰጠ፣ የማን ቤት በምን አይነት እምነበረድ እንደተሰራ፣ ዝርዝር አድርገው የሚነግሯችሁ አሉ። ህዝቡ ሁሉን ዘርዝሮ አውቃል። ያሁኖቹ ጉዶች ደግሞ ይሉኝታ እንኳን የላቸውም፣ የጄኔራል ማዕረጉን የደረደረ ወታደር መሀል አዲስ አበባ ላይ ቆሞ ቤት ሲያሰራ ታያላችሁ፤ ሚኒስተሩ ትላልቅ ካሚዮን የሚገዛው ከአብራኩ በወጣች ልጁ ስም ነው፤ ሌላም አለቀዳማዊ እመቤቲቱም አስር ቦታ የምታስጀምራቸው ቤቶች ጠሀይ ሞቆታል። ወሎ ሰፈር አካባቢ ታስገነባለች በሚባለው ህንጻ የጦር ሰራዊት የጭነት መኪና የሚገለብጠው አሸዋና ሲሚንቶ… ከሰው አይን ሽፋሽፍት የራቀ አይደለም። ልቀጥል ነው…።