ኢትዮጵያ በዊኪሊክስ ፋይሎች (ሊያነቡት የሚገባ)

በአቢይ አፈወርቅ

ክፍል ሁለት

የወቅቱ ገናና ቃል ‘ሽብር’ ሆኗል። ሹማምንቱ ሳይጠሩት አያድሩም። ህዝቡም ሲያስበው ውሎ ያድራል… ያልተሸበረ ማን አለ?” ያሰኛል። እውነት ነው ህዝቡ ተሸብሯል። እንግዳውን ቤቱ ለማሳረፍ ተሳቋል። መኪናውን ለሰው ማዋስ የማይታሰብ ነገር ሆኗል።… በዚህ ዘመን ‘ሪፖርት አላደረክም’ በሚል በከባድ ወንጀል ሊያስጠይቅ የማይችል ነገር ያለ አይመስልም። እድሜ ለ’ጸረ ሽብር’ አዋጁ!…