የዳዉሮ ዋካ ህዝብ ከአመፅ ወደ እንባ (ክፍል አራት)

የአቶ አለማየሁ አሰፋ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የደቡብ ክልል የፖለቲካ ሃላፊ በደልና ሙስና

የመ/ር የኔሰው ገብሬ መስዋዕትነትና የወያኔ ቅጥፈት

ዋካ (ከስዊድን) [email protected]

በባለፈው ክፍል ሦስት ፅሁፌ ላይ አቶ አለማየሁ አሰፋ በዳዉሮ ዋካ ህዝብ ላይ ያደረሰውን በደል በግልና በቡድን በመደራጀት የፈፀመዉን ሙስናና  ፈርጀ ብዙ ወንጀል በጥቂቱ ለማቅረብ ሞክሬያለሁ። ዛሬ በዋናነት የሰማዕቱን መምህር የኔሰው ገብሬን ህልፈትና ከህልፈቱም በኋላ የተሰራዉን የወያኔ የሃሰት ፕሮፓጋንዳዉን በሚመለከት የተወሰኑ እውነታዎችን አስነብባችኋለሁ።