‹‹አፍሪካ ከካንኩን ጉባዔ መሠረታዊ ለውጥ አትጠብቅም›› ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ

(በጥበበ ሥላሴ ጥጋቡ)

ከወራት በኋላ በካንኩን ሜክሲኮ በሚደረገው የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ድርድር ከኮፐንሀገን የተሻለ ሊሆን እንደሚችል፣ ከትናንት በስቲያ በአፍሪካ ኅብረት በተደረገው የአፍሪካ አገሮችና መንግሥታት መሪዎች የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ተገለጸ፡፡