የጸረ ኤድስ የገንዘብ ድጋፍ መቀነስ በአዲስ አበባው የኢካሳ ጉባዔ አቢይ ትኩረት እንደነበር ተገለጠ

በዓለም ላይ ለጸረ ኤድስ እንቅስቃሴዎች የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ መቀነስ ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ በተጠናቀቀው ጉባዔ ጎልቶ የወጣ አጀንዳ እንደነበር የኢትዮጲያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አስታወቁ ። የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በተለይ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በጉባዔው ከአስር ሺህ በላይ ተሳታፊዎች መገኘታቸውንና የተሳካም እንደነበር ገልጠዋል። ሚኒስትሩን ያነጋገራቸው እስክንድር ፍሬው ተከታዩን ዘገባ ከአዲስ አበባ አስተላልፏል።