የሲያትሉ ስብሰባና የጫረው ጥያቄ!! (ኣረጋዊ በርሀ – ዘ ሄግ)

የኢትዮጵያዊያን ህዝባዊ ፎረም በሲያትል ምስጋና ይድረሰውና፤ “በ ገራችን ዘላቂ ሰላም፤ ዲሞክራሲና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አንድነት ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት ማስተባበር ለምን አልተቻለም? ” በሚል መርሃ-ርዕስ የተለያዩ ተቃዋሚ ድርጅቶች አሰባስቦ በ12/11/2011 ዓ.ም.ፈ. ከህዝብ ፊት ማከራከሩ ወይም ማወያየቱ ይታወሳል።

 

በዚህ የሲያትል ውይይት መድረክ ዶ/ክ ብርሃኑ ነጋ የግንቦት-7ን፤ ኣቶ ኣሚን ጁንዲ የኦነግን እና እኔ ደግሞ የኢዴሃሕ (የህብረቱ)ን አቋም ከህዝብ ፊት አቅርበን በመካከላችን ባሉት ልዩነቶች ላይ ክርክር እንድናካሂድ የተዘጋ  ነበር ። ህዝቡም ክርክሩን ተገንዝቦ ትክክለኛ የመሰለው አቋም ላይ ድጋፉን ወይም ተቃውሞውን እንዲሰጥና የጋራ የሆነው ሃገራዊ ራዕይን እንዲያዳብር ሁኔታዎችን ለማመቻቸትም ነበር። በእቅዱም መሰረት ድርጅቶቹ ለብዙ ጊዜ ያደበሩትን አቋም በፁሁፍ መልክ አቅርበው ህዝቡም የመሰለውን ጥያቄና ኣስተያየት በመሰንዘር ለሶስት ሰዓታት የዘለቀ ውይይት ተካሂደዋል።

 

በድርጅቶቹ የቀረበው ገለፃ ከተጠበቀው በላይ ጊዜ ቢወስድም ተሳታፊው ገለፃውን ካዳመጠ በኋላ ተከታታይ ጥያቄዎችን በማንሳት ግልፅ ባልሆኑ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራሪያ እንዲሰጥበት አድርጓል። ለክርክሩ የተመደበው ጊዜ በማነሱና ድርጅቶቹ እርስበርስ ሳይጠያየቁ በመቅረታቸው የተነሳ ተሳታፊው የዚህ ዓይነት ክርክር በስፋትና በጥልቀት እንዲቀጥል ለፎረሙ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

 

ይህ በሲያትሉ ፎረም የተ መረው ኣዲስ የክርክር ባህል ለሁሉም ኢትዮጵያዊ አበረታች ዜና መሆኑ ቢታወቅም ቅሉ ኣንዳንድ ጥያቄዎች ደግሞ መጫሩ አልቀረም። ከነዚህ ውስጥ በዋናነት ላነሳው የፈለኩት ጥያቄና ግልፅ መሆን ያለበት ጉዳይ “ህብረቱ ከማንኛውም ተቃዋሚ ድርጅት ጋር ያለ ቅድመ-ሁኔታ ለመደራደር ዝግጁ ነው” ሲሉ አንዳንድ ዘጋቢዎች የሰጡትን አስተያየት ይመለከታል። ይህ አባባል ትልቅ ጉድለት ያለበት ወይም የተዛባ ኣስተያየት ከመሆኑ የተነሳ ህብረቱም የማይደግፈው መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

 

በቅድሚያ ከተለያዩ ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር በህዝብ ፊት ቀርቦ በአቋም ላይ ክርክር ማካሄድ በአንድ በኩል፤ ከሁለት ወይም ሶስት ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመስራት ወደሚያስችል ድርድር መግባት በሌላ በኩል ፍፁም የተለያዩ ጉዳዮች መሆናቸው ግልፅ ሊሆን ይገባል ፣ የፊተኛው ወደ ሁለተኛው ሊያመራ ወይም ሳያመራ ሊቀር እንደሚችል እንዳለ ሆኖ ማለት ነው ::

 

የኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት መቀበል ጉራማይሌ አመለካከት ላለው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ ለሚያሰራ እቅድ የድርድር ቅድመ-ሁኔታ ከመሆኑ በላይ የማንነትና የህልውና ታሪካዊ መሰረት መሆኑ ሊታወቅ ያስፈልጋል። አለዚያ የጋራ ድርድሩ ሰማይ ላይ ተንጠልጥሎ ሊካሄድና ተጨባጭ ሊሆን አይችልም። (ህብረቱ ከዚህ በፊት ኡትሬክት ላይ የወሰደው አቋም ይሄን ያስታውሰናል)። ይህ ቅድመ-ሁኔታ በኦነግም ይሁን ግንቦት-7 ለተለያዩ ምክንያቶች ተቀባይነት እንደሌለው በተደጋጋሚ የተገለፀ ቢሆንም አማራጩ ምን ሊሆን እንዲመችል በአሳማኝ ሁኔታ ማቅረቡ ይጠበቅባቸዋል። በዚህ ርእሰ-ጉዳይ ላይ ህዝብ ፊት በመከራከር የህዝቡን ድምፅ እንደአስታራቂ ሃሳብ መውሰዱ መፍትሄ ሊሆን ይችላል እላለሁ።

 

ሌላው አከራካሪ ሆኖ የቀረበው ነጥብ በኦነጉ ተወካይ በአቶ አሚን ጁንዲ የቀረበው የመገንጠል ጥያቄን የሚኮንን አቋም ነው። አቶ አሚን “ኦነግ የመገንጠል ጥያቄ አላነሳም አሁንም አያነሳም” ሲሉ ይህን ጥያቄ ከፕሮግራማቸው ኣንስተው_ኣላነሱ እንደሆን ኣለመግለጸቸውና ድርጅቱ የያዘው ኣ ንዳ በኣንዲት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ውስጥ የመኖር እንደሆነ በግልጽ ኣልተቀመጠም። በግልጽ መቀመጥ እንዳለበት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ፍላጎት ሆኖ እያለ የመገንጠልን ጥያቄ ውድቅ የሚደርግ አባባላቸውን አንዳንድ ወገኖች በጸጋ ሲቀበሉትና ብርታት እንዲያገኝ ሲደግፉት፤ ሌሎች ደግሞ ኦነግ እስካሁን በይፋ ሲያራምድ ከነበረው አቋም ጋር በማያያዝ ግልጽነትና እውነትነት የጎደለው ነው ሲሉ አውግዘውታል። ሁለቱም ግላዊ ግንዛቤዎች እንዳሉ ሆነው የአቶ አሚንን ይፋዊ አቋም በፀጋ ተቀብሎ በመደገፍ ወደ እማያሻማና ከፍ ያለ ደረጃ እንዲደርስ መገፋፋት ለሁሉም ጠቃሚ ነው ስል፤ ይፋዊ አቋሙን በጥርጣሬ አይን የሚያዩት ሰዎች ያነሷቸው ጥያቄዎች ግልፅ የሆነ መልስ ያገኙ ዘንድ ዝርዝር መግለጫ መጠየቅ ወይም ሌላ ህዝባዊ የክርክር መድረክ ፈጥሮ እቅጩን ማወቅ ይጠበቅባቸዋል።

 

በመሰረቱ በህዝብ ፊት ግልፅ ክርክር ማካሄድ ሃሳቦች እንዲብላሉና አቋሞች ነጥረው እንዲወጡ ይረዳል እንጂ ክፋት የለውም። በየጓዳው አድፍጦ ሃሳቦች መወርወር (ላለፉት 20 ዓመታት እንደተገነዘብነው)፤ በባዶ ሜዳ የስደት መንግስት ይመስረት ማለትና የመፃፍ ችሎታ ማሳየት ክፋት ባይኖረውም ቅሉ ለሃገራችን የሚበ ው የስርዓት ለውጥ ሊያስገኝልን እንዳልቻለ ኣከራካሪ ኣይመስለኝም። የጎደለው በህብረት መታገልና ማታገል ነው:: የአንድን ሃሳብ ሃያልነት የሚመዘነው ደግሞ በመሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር ያለው ተዛማጂነት በማስረገጥና ተቀናቃኝ ከሆነው ሃሳብ ጋር ፊት-ለፊት ተላትሞ የብዙሃኑ እምነት ሆኖ ነጥሮ ሲወጣ ነው።

 

በዚህ ረገድ የሲያትሉ ፎረም ይህን ገንቢ ስራ  ምሮታል ማለት ይቻላል። ጅምሩ አበረታች ሆኖ እያለ ግድፈት ኣልነበረበትም ኣይባልም። የተወሰኑና አንኳር በሆኑ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ብቻ ትኩረት ሰጥቶ ሰብሰባውን ማካሄድና ማጠቃለል እንደነበረበት መጠቆም እወዳለሁኝ። በማያያዝም ሌሎች ወደፊት የሚዘጋጁ የኢትዮጵያዊያን መድረኮች ከሲያትሉ ፎረም ብዙ ሊማሩ እንደሚችሉና ትስስር በመፍጠር የትግላች ኣድማስ ማስፋት እንደሚጠበቅባቸው በአህፅኖት መግለፅ እወዳለሁኝ፡፡

 

በበኩሌ የምለው ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚመለከተው አንኳርና መሰረታዊ ጥያቄ ህዝቡ የሚቆጣጠረው መንግስታዊ ሥርዓት (state) የመፍጠር ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያችን ከኩሻይት ዘመን ኣንስቶ የመንግስታዊ ሥርዓት (state)  ማሪ ጥንታዊት ሃገር ብትሆንም አሁን ኣጣብቂኝ ውስጥ የገባችው ህዝቡ በራሱ የመሰረተውና የሚቆጣጠረው መንግስታዊ ሥርዓት በማጣትዋ ነው። ይህንን ዓይነት የጋራ ስርዓት እንዳያቆጠቁጥ እንቅፋት የሆኑት ኣመለካከቶችና ሃይሎች ተወግደው የጋራ ስርዓቱ እንዲያንሰራራ በዚህ የጋራ ርዕስ ዙሪያ ሁሉም ኢትዮጵያዊ (በፖለቲካም ሆነ በሲቪክ የተደራ ና ያልተደራ ) መከራከርና የጋራ ንድፈ ሃሳብን በማያሻማ ሁኔታ መንደፍና ለተግባራዊነቱ በድርጅት ቅርፅ ምእኩል ህብረት ኣበጅቶ መታገል ይኖርበታል። በዚህ መልክ መራመዱ ከተዘበራረቀ የትግል አካሄድ እንድንድንና ቅደም ተከተሉን የጠበቀ የትግል ውጤት እንድናስመዘግብ ይረዳናል እላለሁ።

 

የወቅቱ ህብረት ከፓሪስ-1 (1993 ዓ.ም.ፈ)  ምሮ እያዳበረ የመጣው የህዝባዊ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት ህንፀትና የእኩልነታዊ አንድነት ምስረታ አቋሙ አሁንም ሊያሰራ ይችላል። ምናልባት እንከን አለበት የሚል ወገን ካለም አማራጩን ይዞ፤ በህዝብ ፊት ቀርቦ መከራከር ሃገራዊ ግዴታው መሆኑ ህብረቱ ደጋግሞ ኣዘክረዋል። በዚህ መልክ የተ መረው ክርክራችን ከቀጠለ በግልፅና በበሰለ ኣኳኋን ወደ ተጨባጭና ሊያሰራ ወደሚችል ድርድር መሸጋገር ይቻላል።

 

01 / 12 / 2011