መቀመጫውን ካሊፎርኒያ ያደረገው የኦክላንድ ኢንስቲቲዩት በአሁኑ ወቅት የወያኔ አገዛዝ እየፈፀመ ያለውን ህብረተሰቡን የማፈናቀልና መሬቱን በርካሽ የመቸብቸቡን ድርጊት ኮነነ:: 75 በመቶ የመሬት ኢነቨስትመንት ዘርፉም በትግራይ ተወላጆች መያዙን ይፋ አደረገ
የኦክላንድ ኢንስቲትዩት ዳይሬክር አኑራዳ ሚታል፣ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ልዩ የቃለመጠይቅ ቆይታ ድረጊቱ ህገወጥና በአፋጣኝ መቆም የሚኖርበት ነው ሲሉ አሳስበዋል።
ይህ የመሬት ችርቸራ ለምግብ ፍጆታ የሚውል እህልን ለማምረት በሚል ሰበብ ለውጭ ኢንቨስተሮች ሲሰጥ በኖረበት መሬቱ ላይ ሀሳብ እነዲሰጥ እነኳን ያልተጠየቀው ህብረተሰብ፣በህይወቱ ላይ ትልቅ ቀውስ እነደተፈጠረበት ነው የተናገሩት። « የውሀ አቅርቦትን አካቶ እየተሸጠ ያለውን የለም መሬት ዋጋ ብናይ የአካባቢውንና የማህበረሰቡን ሁኔታ በፍፁም ከግምት ውስጥ ያስገባ አለመሆኑን መረዳት ይቻላል፣ ይህም የሚያሳየው የኢትዮጵያ መንግስት አቅም የለሹ ተፈናቃይ ህብረተሰብ ላይ እየተከሰተ ያለውን ችግር ከቁብም አልቆጠረውም » ብለዋል።
በኢትዮጵያ መሬት በመንግስት ቁጥጥር ስር ስለሚገኝ ከህብረተሰቡ ጋር የመደራደርያ መነሻ መብት እንኳን አለመኖሩን አውስተዋል። በዚህ አመት ኦክላሀማ ዩንቨርስቲ በአለማችን እየተካሄደ ባለው መሬት ችርቸራ ሰበብ ችግር ላይ ስለወደቁት ሀገራት ባወጡት ልዩ ሪፖርት፣ ኢትዮጵያን በተመለከተ፣ የመሬት ሊዝ ይዞታ በሀገሪትዋ ያለውን የምግብ እጥረት ያባብሰዋል ፣በስነምእዳር ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ይኖረዋል፣ ሀገሬው ህብረተሰብንም ዘሩ እነዲጠፋ የሚያደርግ ነው ብሎለታል።
ምንም እንክዋን መለስ ዜናዊ በሚሊዮን የሚቆጠር ሄክታር መሬት በሊዝ የማደሉ ሂደት በምግብ እራሳችንን ለማስቻል ይረዳናል እያለ የሚከራከር ቢሆንም ኦክላማ ግን በተቃራኒው ረሀብና ድርቅን የሚያባብስ ነው ሲል በጥናቱ ለማሳየት ሞክሯል። ከዚህ አልፎ ይህ ድርጊት የህዝቡን መሰራታዊና ሰብአዊ መብት የጣሰ መሆኑንም አሳይቷል።
ይህንን የተቃወሙ የህብረተሰቡ ክፍሎቸም እንደእንስሳ እየታደኑ የድብደባና የአስገድዶ መድፈር አሰቃቂ አደጋ እየደረሰባቸው ይገኛል፣ በተደጋጋሚ የመሬት ሊዝ ሰለባ የሆነው በጋምቤላ ክልል የሚገኘው የጋምቤላ ብሄራዊ ፓርክም ባሁኑ ወቅት ካርቱሪና ሳውዲ ስታር በተባሉ በሼክ መሀመድ አላሙዲን ባለቤትነት በሚታወቁ ካምፓኒዎች ደኑ ተጨፍጭፎ፣ ወድሞ በቁጥጥራቸው ስር መዋሉ ታውቋል።
ሌላው በግርምት የሚያስደምመው ጉዳይ ደግሞ በጋምቤላ ከተያዘው ሰፊ መሬት ውስጥ 75 በመቶ የሚሆነው ከህወሃት ጋር ቁርኝት ባላቸው የትግራይ ተወላጆች መሆኑ ነው። እንደ ኦክላማ ኢንስቲቲዩት ጥናት በጋምቤላ አገሬውን አፈናቅለው መሬት የተቸራቸው የትግራይ ተወላጆች ፤ ወለድ የማይከፈልበት የብድር አገልግሎት ከመንግሥት ባንኮች እየተመቻቸላቸውና የያዙትን ቦታ ያለምንም ክፍያ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን በአካባቢው ያሉትን ኢንቨስተሮች ተዘዋውሮ ያነጋገሩት የኦክላንድ ኢንስቲቲዩት ዳይሬክር አኑራዳ ሚታል አረጋግጠዋል።
የዳይሬክተሯን የአኑራዳ ሚታልን ምስክርነት የሰሙ ኢትዮጵያዊያን ባረጉት ግምገማ ፤ የሥር ዓቱ ደጋፊ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች በተለያዩ ክልሎች በመሄድ መሬት እንዲይዙና ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚበረታቱበት ዋናው ምክንያት በ እጃቸው የገባውን የፖለቲካ ስልጣን መከታ በማድረግ ኢኮኖሚውን በመቆጣጠር ስልጣናቸውን እስከወዲያኛው እናዘልቃልን በሚል ስሌት ነው ብለዋል።