የወያኔ አምባሳደር ውሎ በዳላስ ከተማ

ቅዳሜ ኖቨምበር 12፣ 2011 በዳላስ ከተማ የወያኔ መንግሥት አምባሰደር “ደጋፊዎቼ” ናቸው የሚላቸውን ኢትዮጵያኖችን ሰብስቦ የቦንድ ሺያጭና የኢንቨስትመንት “ውይይት” በሚል ሽፋን የተከናወነውን ተግባር አንድ ኢትዮጵያዊ በስብሰባው ውስጥ በአካል ተገኝቶ ያጠናከርነውን ዘገባ

1. የስብሰባው ተሳታፊዎች ምስል (profile) ምን ይመስላል?
2. ስለ ግንባር ቀደም የቦንድ ገዢዎች ማንነት የተገነዘብነው
3. አምባሳደሩ ያስየማቸው የከተማው የወያኔ “እንደራሴዎች” ስም ዝርዝርና ከአምባሳደሩ የተሰጣቸው መመሪያ በሚሉ ርዕሶች ከፍለን እናካፍላችኋለን።

ስብሰባው የተኪያሄደው በ 15201 Dallas Parkway, Addison, TX 75001 በሚገኘው InterContinental Hotel ውስጥ ነው። የመጀመሪያው አስገራሚ ነገር በወያኔ አምባሳደር ለኢትዮጵያውያን ተብሎ የተጠራው ስብሰባ የቁጥጥር ዓይነት ነው። ከሰላሳ እስከ አርባ ሺ ኢትዮጵያውያን የሚገኙበት ከተማ ውስጥ የስብሰባው ታካፋዮች የተጠሩት አዘጋጆቹ በሚያቋቸውና በሚያምኗቸው ሰዎች ውስጥ-ለውስጥ በተሸጡ ቲኬቶች መሠረት ነበር። እያንዳንዱ ትኬት ያዥ በተለይ ትኬት ያዡ በግልጽ የሚታወቅ የነሱ ደጋፊ ካልሆነ በር ላይ ቲኬቱን ከማን እንደገዛ ሰም እየሰጠ ነበር የሚገባው። በዚህ መንገድ የተሰበሰበው ተሰብሳቢ ምን እንደሚመስል ግልጽ ነው። በእኛ እይታ የስብሰባው ተካፋዮች ሦስት ዓይነቶች ናቸው።

የስብሰባው ተሳታፊዎች ምስል (profile) ምን ይመስላል?

አንደኛውና በቁጥር በጣም አብላጫ ያለው ተሰብሳቢ የመጣው ከከተማውና ከአካባቢው ከሚገኙት የትግራይ ኮሚኒቲዎች ነበር። ሁለተኛውና በሚቀጥለው ደረጃ አብላጫ ያለው ክፍል ደግሞ የወያኔ የከፋፍለህ ግዛ የወቅቱ ሰለባ የሆኑ የህበረትሰባችን ጥቂት ክፍሎች ነበሩ። ሦስተኛውና የመጨረሻው ክፍል መድረኩን ይዞ ስብሰባው የወያኔ ደጋፊዎች ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያውያን ነው ለማስኘት ሽፋን ሰጭ የሆነው ክፍል ነው። በቁጥሩ በጣም አናሳ በሰብሰባው ላይ ግን ሆን ተብሎ አብላጫውን ሚና የተጫወተው ይሀው ክፍል ነው። ቡድኑም አንድ የመከነ ፖለቲከኛ ፤ አንድ የታወቀ የከተማው አምታቺ ጉረኛ፤ የመሬትና ሌላም ንበረት ፍለጋ በግላቸው ሳይሆን በመንግሥት ግንኙነት በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚመላለሱ በደንብ የታወቁ ደጅ ጠኚዎችንና የመሳሰሉትን ሰዎችን የያዘ ነበር። ደጋግመን የወያኔ ታላላኪዎች ወደ ከተማችን ሲመጡ ግልጽ እየሆነ የመጣልን ነገር የወያኔ የዲያስፖራ መሰረቶች የነዚህ የሶስት ክፍሎች ጥምር ነው። ለወደፊቱ በዚህ ጉዳይ ላይ በአሃዝ የተመሰረተ ዝርዝር ለማቅርብ ቃል እንገባለን። በሌሎች ከተሞች ያሉ ኢትዮጵያዊያኖችም በዚህ ሁኔታ ላይ ተመሳሳይ ምስል (profiling) እንዲያደርጉ እንጠይቃለን። ይህንን በማድረግ የወያኔን የዲያስፖራ ደጋፊዎች የዘር፤ የጠባይና የሞራል ይዘት በአሃዛዊ ማሰረጃ በማጋለጥ የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ጥረት ማክሸፍ እንችላለን።

ስለ ግንባር ቀደም የቦንድ ገዢዎች ማንነት የተገነዘብነው

በስብሰባው ውስጥ ቦንድ የገዙት ዋናዋና ሰዎች የስም ዝርዝር ለጊዜው ይፋ ባናደርገውም የሁሉም የስም ዝርዝር አለን። የገንዘብ አውጪዎችን ማንነነት በደንብ ስለምናውቅ ገንዘቡ ሰዎቹ በገዛ አገራቸው አሁንም ሆነ ገና ወደፊት እናፈራዋለን ለሚሉት የመሬት ይዞታና የቤት ግንባታ ወያኔ መሉ በሙሉ በሚቆጣጠረው የመሬትና የኢኮኖሚ ሀገር ውስጥ የማለሳለሻ ግቦ እንደሆነ ግልጽ ነው። ለምሳሌ በብዛት የስብሰባው ተካፋይና ከመጀመሪያው ጀምሮ የወያኔ ደጋፊ የሆኑት ትግራዮች ትንሽ ወይም ምንም ቦንድ ሳይገዙ፤ ቤት ዘግተው ወያኔን የሚያሙት ሁለት ሰዎች ግን በ በብዛት ቦንድ ሲገዙ ታይተዋል። አንዱ የቦንድ ገዢማ ስሜ እንዳይገለጽ ሲል ተሰምቷል። ማንን ፈርቶ ነው ስሜ እናዳይገለጽ የሚለው? ለመንግሥት ገንዘብ መስጠት ከሕዝብ፤ ከዘመድ አዝማድና ከጓደኛ ካልሆነ ከማነው የሚሸሸገው? እነዚህ “ለጋሾች” ገንዘባቸውን ያወጡት የወያኔን ቦንድ ገዝተው ለማትረፍ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። የ50% የዋጋ ንረት ባለበት አገር ውስጥ በ 5% ና በ10% ወለድ ቦንድ መግዛት እንደማያዋጣ ያውቃሉ። አባይም በወያኔ ይገደባል ብለው ለፍተው ያገኙትን ገንዘባቸው እንደማይቆምሩበት ይታወቃል።

እንደሚመስለን “እናቴን ያገባ ሁሉ አባቴ ነው” በሚል የጥገኝነትና የፈሪ መንፈስ ሀገሬ ውስጥ ጥሪት ለማፍራትና ሀገሬ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት ለመደሰት ለወያኔ መገበር አለብኝ የሚል የፈሪና የስግብግብ ብልጣብልጥነት ዘዴ እናያለን። ይህ መቼም ከሞራል ቅሌቱ ሌላ ፍሬ ያለው ብልጣብልጥነት አይደለም። የወያኔ መንግሥት የሸጠውን የወደፊት ቦንድ ቀርቶ በሚቀጥሉት ጥቂት አመታት ቃል የገባውን ልፈጽምም ቢል እንኳን እድሜ የለለው መንግሥት ነው። በአካባቢያችን ከሱ የገዘፉና አንነኬ ነን ባዮቹ ሙባረክና ጋዳፊ ሳይቀሩ የታሪክ ትቢያ ሆነዋል። የትግሬ ነፃ አውጪ ወያኔዎችም መንግሥት ከዚህ እጣ እንደማያመልጥ ለሁሉም ግልጽ እንዲሆን ይገባል። ለነዚህ ወገኖቻችን የምናሳስበው ህዝባችሁና አገራችሁን በዚህ በመከራ ጊዜ ሌላው ቢቀር ከጠላቷ ጋር ሳትተባበሩ ለማለፍ አርቆ ማየቱ እንዲኖራችው ነው።
አምባሳደሩ ያስየማቸው የከተማው የወያኔ “እንደራሴዎች” ስም ዝርዝርና ከአምባሳደሩ የተሰጣቸው መመሪያ
ከዚህ ስብሰባ በዋናነት ያገኘነው ነገር አምባሳደሩ አፉን ሞልቶ በአደባባይ የወከላቸው የወያኔ የከተማችን የብጥበጣ ተጠሪዎች እነማን እንደሆኑ ማወቃችን ነው። በዳላስ ከተማ የወያኔ ታማኝ ሚስጥረኛና ተጠሪዎች በትግራይ ኮሚኒቲ ውስጥ ያሉ አባላቱ እንደሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን። ከዚህም በተጨማሪ የከተማችን ትግራዮች የራሳቸውን ኮሚኒቲ ማህበር፤ የራሳቸውን ቤተ ክሪስቲያንና የባሀል ተቋማት ይዘው በሰላም እየኖሩ፤ በዳላስ የሚገኘውን የተቀረውን ኢትዮጵያዊ ግን በየማህበሩና ቤተ ክሪስቲያኑ እየገቡ እንዲበጠብጡ በዚህ ስብሰባ ውስጥ በወያኔ አምባሳደር በግልጽ መመሪያ የተሰጣቸው ሦስቱ ቀንደኛ ተወካዮች የሚከተሉት ናቸው፡
1. አብይ መኮንን (በሰብሳቢነት የተሰየመ፤ ለጥቅሙ ምንም ከመሸጥ የማይመለስ የታወቀ እበላ-ባይ)
2. ተኮላ (የመከነው ፖለቲከኛ፤ በዳላስ ከተማ የሚኪያኤል ቤተክሪስትያን ከሳሽ፤ በስብሰባው ዕለት ዋነኛ አስተባባሪና የእለቱ ግጥም አንባቢ)
3. ተክሉ ብርሃኑ (የቡድኑ ዕውነተኛ መሪ የትግራይ ተወላጅ)

አምባሳደሩ እነዚህንና ሌሎች ስማቸውን ለመጥቀስ ያልፈልግናቸው እበላ-ባዮች ቆሞ ካሰየመ በኋላ በሰጠው መመሪያ ከአሁን ጀምሮ ይህ ቡድን እሱን ወክሎ በዳላስ ከተማ እንዲንቀሳቀሱ ፈቅዷል። በዚህ መመሪያው መሰረት ቡድኑ ከዚህ በፊት እንደሚያደርገው ኢምባሲ እየደወለ ይህንን እናድግ ወይስ አናደርግ እያለ መጠየቁን አቁሞ በራሱ ተነሳሽነት በከተማው የወያኔን ሥራ መስራት አለበት ሲል አስጠንቅቋል። ከሁሉም በላይ አንባቢዎቻችን እንዲረዱት የምንፈልገው ግን አምሳሳደሩ በዳላስ ከሚኖረው በብዙ ሺ የሚቆጠር ኢትዮጵያውያን ብዛት አንጻር በስብሰባው የተእኘው ሰው በጣም ትንሽ እንደሆነ ተናግሮ ለወደፊቱ ከዚህ በላይ ሕዝብ እንዲሰበስቡለት ቆሞ ላሰየማቸውን ወኪሎቹ አሳስቧል። ይህንን ለማሳካትም በከተማው በሚገኙ ቤተክሪስትያናት፤ መስጊዶች፤ እድሮችና የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማህበራትን በሀገር ቤት ባሉ የብዙሃን ማህበራት እንደሚያደርጉት በ”አስመራጣቸው” ወኪሎቹ ቁጥጥር (በአምባሳደሩ ቃል umbrella) ሥር የሚውሉበትን መንገድ መፈለግ እንዳለባቸው በግልጽ መመሪያ ሰጥቷል።
በነገራችን ላይ በቁጥር ሁለት ላይ ስሙ የተጠቀሰ ተኮላ ና አንዱ የቦንድ ገዤ ግለሰብ በዳላስ ከተማ የምትገኘውን የሚኪያኤል ቤተ ክሪስቲያን ፍርድቤት ከሰው እስከ አሁን የቤተ ክሪስቲያኗንና የምእመናኑን ገንዘብ በከንቱ እንዲባከን ከማድረግ ሌላ አማኙን ሕዝብ በሆነ ባልሆነው ነገር የሚርብሹ ሰዎች ናቸው። ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ ቀንደኛው ተኮላ በዚህ ስብሰባ ላይ በገሃድ የወያኔ የከተማ ተወካይ ሆኖ ሲሰየም ባይናችህ አይተናል፤ በጆራችንም ሰምተናል። ሰለዚህ በዳላስ ከተማ የምትገኙ የሚኪያኢልም ሆነ የሌሎች ቤተ ክሪስቲያናት ምዕመናንን ይህንን የወያኔ እንደራሴዎች ገሃድ የወጣ የብጥበጣ ሥራ አጤናችሁ እንድትገነዘቡ እንጠይቃለን።

በተረፈ የወያኔ አምባሰደር በጠራው ስብሰባ ላይ የተገኛችሁትን በጅምላ ሳይሆን ከዚህ በላይ ስማቸውን የዘረዘርናቸውን በአደባባይ የወያኔን ባጅ የተቀበሉ ተወካዮችን ብቻ ልናሳስብ የምንፈልገው ከአሁን በኋላ እናንተን በጽኑ ክትትል አስገብተን ከወያኔ ጋር ያላቸሁን ማንኛውንም አይነት ግንኙነት ለሕዝብ ይፋ እንደምናደርግ ነው። ከዚህ ተርፎ ደግሞ ከወያኔ ጋር በምትሰሩት ሥራ ሳቢያ አንድም ሰው እዚህም ሆነ አገር ቤት አደጋ ላይ ቢወድቅ በሕግ ተከታትለን በቅርቡ የሶሪያ መንግሥት ሰላይ ላይ እንደደረሰው ዓይነት ውርደት እንደምናስገባችሁ እወቁት። ከዚህም ሌላ በከተማችን ከአሜሪካ መንግሥት ጥገኝነት ጠይቆ የሚኖር ኢትዮጵያዊ እነዚህ ሰዎች በሚጠሩት ስብሰባም ሆነ በሌላ መንገድ ሲተባበር ብናገኘው ለሕግ እንደምናቀርበው አትጠራጠሩ።

በመጨረሻም በስብሰባው ውስጥ የወያኔን አምባሰደር ሀገሪቱ ውስጥ ስለሰፈነው ልክ ያጣ ሙስና፤ የመብትና የነፃነት አፈንና እንዲሁም በቅርቡ የሀገሪቱን ሕዝብ በሙሉ (እበላ-ባዮችንም ጨምሮ) የመለሰ ዜናዊ የትግራይ አገዛዝ ጪሰኛ ስላደረገው የመሬት ፖሊሲ በመጠየቅ አምባሳደሩን ያፋጠጣችሁትንና የስብሰባው አዘጋጆችን ህሊና የሚኮረኩር ውይይት በመጠኑም ቢሆን እንዲነሳ ላደረጋችሁ ዕውነተኛ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንኮራባችኋልን እንላለን።
የወያኔን በኦፊሴል የተረጋገጡ ወኪሎች እንወቅ! አውቀንም ማህበሮቻችንን ከእኩይ ተግባራችው እንከላከል!!
በዳላስ ከተማ ተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያን ነን