የራያ ቢራ ባለአክሲዮኖች በቢጂአይ መግባትና በብሩቴክ መውጣት ላይ ጥያቄ አነሱ

– ቀሪው አክሲዮን ለባለአክሲዮኖች ብቻ እንዲሸጥ ተወሰነ

በቀድሞው ኤታማዦር ሹም ሌተና ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሳዔ ዋና አደራጅነትና ቦርድ ሰብሳቢነት የሚመራው የራያ ቢራ አክሲዮን ማኅበር በአገሪቱ የቢራ ገበያ ውስጥ የሚጠብቀውን ውጊያ በድል ለመወጣት ቢጂአይ ኢትዮጵያን መያዝ አስፈላጊ መሆኑንና የጀርመኑ ኩባንያ ከአክሲዮን ባለድርሻነት የወጣው መክፈል የሚገባውን 3.7 ሚሊዮን ዩሮ ሊከፍል ባለመቻሉ መሆኑን ገለጹ፡፡