ጉባዔተኞቹ የኤድስ ፈንድ የት እንደገባ በሰላማዊ ሠልፍ ጠየቁ
• አካል ጉዳተኞች ቅሬታ አሰሙ
ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ተውጣጥተው በሚሌኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ባለው የኤችአይቪ/ኤድስና የአባለዘር በሽታዎች ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በአፍሪካ (አይካሳ) ጉባዔ ላይ የሚሳተፉ በርካታ ሴቶች፣ በአፍሪካ ለኤችአይቪ/ኤድስ መቆጣጠሪያና መከላከያ ፕሮግራም እንዲውል ከልዩ ልዩ የዓለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች የተሰጠው ገንዘብ የት እንደደረሰና ምን ላይ እንደዋለ ኅዳር 25 ቀን 2004 ዓ.ም. ባካሄዱት ሰላማዊ ሠልፍ ጠየቁ፡፡