በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት የስዊድን ጋዜጠኞች መከላከያ ምስክር ማሰማት ጀመሩ

–    ‹‹ለፖሊስ የሰጠውን ቃል በፊርማው አረጋግጧል የተባለው ስህተት ነው›› ፎቶ ጋዜጠኛ ጁሃን ፐርሰን

በሰኔ ወር 2003 ዓ.ም መጨረሻ የሶማሌ ክልል ልዩ የፖሊስ ኃይል፣ በሽብርተኝነት ከተፈረጀውና ራሱን የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) እያለ ከሚጠራው የሽምቅ ተዋጊዎች ጋር ባደረገው ውጊያ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ፣ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞች፣ በትናንትናው ዕለት የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ማሰማት ጀመሩ፡፡