የደቡብ ሱዳን ህዝበ ውሳኔና የአቢዬ ዕጣ ፈንታ

አሜሪካ ከትላንት በስቲያ ይዛ ብቅ ያለችው የመፍትሄ ሀሳብ ዋንኛዋን አጨቃጫቂ ቦታ የሚመለከት ነው–አቢዬን። በደቡብ ሱዳን ጥር 9/2010 ህዝበ ውሳኔ ይካሄዳል ተብሎ በመጠበቅ ላይ ቢሆንም በነዳጅ ዘይት በከበረችው አውራጃ አቢዬ ፤ ምርጫው የጊዜ ሰሌዳውን ተከትሎ የሚከናወን አይመስልም።