የአይሱዙና የታክሲ ባለንብረቶች የሦስተኛ ወገን መድን ዋስትና ክፍያ ከአቅማችን በላይ ነው አሉ
– ከ150 ሺሕ በላይ ተሽከርካሪዎች የመድን ዋስትና ገብተዋል
የዛሬ ሣምንት ታሕሣሥ 1 ቀን 2004 ዓ.ም. ተግባራዊ መሆን የሚጀምረውን የሦስተኛ ወገን የመድን ዋስትና አዋጅን ተከትሎ የተጠናው የአከፋፈል ሥርዓት፣ አቅማቸውን ያላገናዘበና የበዛ መሆኑን በመግለጽ የአይሱዙና የታክሲ ባለንብረቶች መክፈል እንደማይችሉ ገለጹ፡፡