ደርባ ሚድሮክ መንግሥት 550 ሚሊዮን ብር እንዲከፍለው ጠየቀ
ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የሚድሮክ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ግዙፍ የሆነውና በጥር 2004 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በተገኙበት ይመረቃል ተብሎ ዕቅድ የተያዘለት የደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ ለመንገድ፣ ለኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ፣ ለኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ፣ ለውኃና ለሌሎች መሠረተ ልማቶች ያወጣውን 550 ሚሊዮን ብር መንግሥት እንዲከፍለው ጠየቀ፡፡