ሰበር ዜና ፡ በግንቦት 7 ፍርደኞች ላይ የተጠየቀው የሞት ቅጣት ውድቅ ተደረገ

– የብ/ጄ ተፈራ ማሞና የአቶ አሳምነው ጽጌ ንብረት ይወረስ ተባለ
– በነፃ የተሰናበቱት አራት ግለሰቦች ጥፋተኛ ተባሉ

(በታምሩ ጽጌ)

የሥር ፍርድ ቤት ያስተላለፈባቸውን የዕድሜ ልክ እሥራት ላይ ‹‹ቅር ተሰኝቻለሁ›› በሚል የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በሞት እንዲቀጡለት ይግባኝ የጠየቀባቸው አምስት የግንቦት 7 ፍርደኞች አቤቱታ ውድቅ ተደረገ፡፡ በነፃ ተሰናብተው የነበሩትን አራት ተከሳሾች ደግሞ ጥፋተኛ እንዲባሉለት በጠየቀው መሠረት ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡