ፍኖት – የኃይማኖት አባቶች ለዜጎች ጥብቅ ጥሪ አስተላለፉ
ሰሞኑን ለዓለም አቀፍ ሰብሰባ ወደ አገራችን የገቡ ግብረ ሰዶማውያን በገንዘባቸው ኃይል በሀገራችን የረከሰና የተወገዘውን በተለይም የቤተሰብ ጠንቅ የሆነውን ወንድ ለወንድ የሚደረግ ሩካቤ ሥጋን ዜጎች አጥብቀው እንዲያወግዙ የኃይማኖት አባቶች ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
እነዚሁ ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ የሆኑ አባቶች በእምነቱ አስተምህሮትና ደንብ መሠረት ፈጣሪ የተናገረው ትንቢት በዚህ ዘመን እየተፈፀመና እየተደረገ ለመሆኑ ለኃይማኖቱ ተከታዮች ብዙም የማያስገርም ቢሆንም ሰሞኑን ለስብሰባ በሚል አገራችን የገቡ ግብረ ሰዶማውያን በገንዘባቸው ለሚያቀርቡት ጥያቄ ሁሉ ዜጎች ምላሽ ባለመስጠት ወይም ባለመተባበር አገራቸውንና እምነታቸውን እንዲጠብቁ ጠንከር ያለ መልዕክታቸውን በፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ በኩል እንዲተላለፍላቸው አጥብቀው ጠይቀዋል፡፡
የኃይማኖቱ አባቶች ዛሬ ታይቶ ነገ ለሚጠፋ ገንዘብና ስጦታ ሲባል በተለይ መንገድ መሪዎች (Guides) ሆቴል ሠራተኞች፣ታክሲና መሰል ትራንስፖርት አቅራቢዎች፣አስጎብኚ ድርጅቶች፣ሴተኛ አዳሪዎች የመሳሰሉት ከፍተኛ ኃላፊነት የሚጣልባቸው ስለሆኑ ነቅተው እንዲከላከሉ የአደራ ቃላቸውን ጨምረው አስተላልፈዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ም/ ቤትን ጨምሮ የበርካታ አብያተ እምነት መሪዎችን በአባልነት የያዘው የኢትዮጵያ የኃይማኖቶች ጉባዔ የግብረሰዶማውያኑን ስብሰባ በመቃወም ሊሰጡት አስበው የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በድንገት በስፍራው በመድረስ እንዲሰረዝ ማድረጋቸው የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃንን ጨምሮ ቪኦኤ የአማርኛው ፕሮግራም መዘገባቸው የሚታወቅ ሲሆን የመንግሥት ጣልቃ መግባትን በተመለከተ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ከሚለው የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ጋር የሚጣረስ ነው የሚሉ የሕዝብ አስተያየቶች ከሁሉም የኃይማኖት ተከታዮች ዘንድ እየተደመጡ ይገኛሉ፡፡ በተለይ ደግሞ ቀደም ሲል የምእመኑን በርካታ ጥያቄዎች በማን አለብኝነት አንሰማም ያሉት የኃይማኖት አባቶች የእነሱም ድምፅ በተራው አልሰማም ማለቱ “ያስቀመጡትን እንዳነሱት ይቁጠሩት” የሚለው ሚዛን ደፍቷል፡፡
የአንድነት ፓርቲ ለሕዝብ መብት መከበር የቆመ፣ በአገር ዉስጥ በሰላም የሚታገል ፣ በአገር ቤት ኢትዮጵያዉያንን ለማደራጀት የሚንቀስቀስ የሰለጠነ ሰላማዊ የፖለቲካ ድርጅት ነዉ። ሕዝቡን ለማስተማርና ለማንቃትም በየሳምንቱ የፍኖት ጋዜጣን አትሞ ያስራጫል። የፍኖት ጋዜጣን በብዛት ለማሳተምና በስፋት በየክልሎቹ ለማሰራጨት ከፍተኛ የገንዝብ አቅም ይጠይቃል። በአገር ቤት ከሚታገሉ ወገኖቻችን ጎን ይቁሙ ! በገንዘብዎት የአንድነት ፓርቲን ይደግፉ !
ፍኖት እትም 19ን በሙሉ ለማንበብ ከዚህ ይጫኑ !