መንግሥት ያጣጣለው የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ሪፖርት

ባለፈው ሰኞ የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች ልዑክ ያወጣውን የመጨረሻ ሪፖርት የኢትዮጵያ መንግሥት ተቀባይነት የሌለው በማለት አጣጥሎታል፡፡በትናንትናው ዕለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን ያወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ሒደት ያላገናዘበና የተሳሳተ የፖለቲካ ግንዛቤን የያዘ በመሆኑ ለሁለተኛ ጊዜ መንግሥት እንደማይቀበለው አስታውቋል፡፡ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በበኩላቸው የኅብረቱ ሪፖርት የፈለጉትን ያህል መረጃ ያላካተተ ቢሆንም፣ የያዘውን መልዕክት የሚደግፉት መሆኑን አስረድተዋል፡፡  የኃይሌ ሙሉ ዘገባ በዚህ ዙሪያ ቅኝት ያደርጋል እዚህ ይመልከቱ፡፡