ፍትሕ ሚኒስቴር ከሼክ አል አሙዲ የባንክ ሒሳብ እንዲከፈለው ተወሰነ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሰባተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ስም ከሚገኝ ሒሳብ 905,158.06 ዶላር ወጪ ተደርጐ  ለፍትሕ ሚኒስቴር እንዲከፈል ህዳር 20 ቀን 2004 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡