በአስካሉካን ባለቤት ላይ ምስክሮች መሰማት ጀመሩ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ የወንጀል ችሎት ለመጀመርያ ጊዜ በአፍሪካ አኅጉር በተዘጋጀው ዓለም ዋንጫ ላይ በርካታ ሰዎችን ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመላክ የገባውን ቃል ባለመፈጸሙ በማታለል ወንጀል በተከሰሰው፣ የአስካሉካን ትሬዲንግ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ግርማይ ገብረ ሚካኤል ላይ ህዳር 20 ቀን 2004 ዓ.ም. የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን መስማት ጀመረ፡፡