ጓደኞቼን መልሱልኝ (ሊያነቡት የሚገባ)

ተመስገን ደሳለኝ

“ሰማዩ ዳምኗ፣ ከበድ ያለ ውሽንፍር የቀላቀለ ካፊያ መሰል ነገር ማንጠባጠብ ጀምሯል። በአጠቃላይ ሲታይ ቀኑ ደስ አይልም።” ይላሉ የልብ ወለድ ጸሀፊያን አንዳንድ ደባሪ ቀኖችል ሲገልጹ። እውነትም ደባሪ ቀን አለና። ለምሳሌ ያሳለፍነው ቅዳሜም እንዲሁ ደባሪ ሆኖብኝ ነው ያለፈው።